Fana: At a Speed of Life!

ምሽት በተደረጉ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት ምሽት በተደረጉ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በምሽት በተካሄደ የእንትሪም ግማሽ ማራቶን በወንዶች ጀማል ይመር 59 ደቂቃ ከ3 ሰከንድ በመግባት አንደኛ ደረጃን ይዞ ሲጨርስ፥ በዚሁ ርቀት ሌላኛው አትሌት ተስፋሁን አካልነው 4ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

በሴቶች ደግሞ ያለም ዘርፍ የኋላው 1 ሰዓት ከ4 ደቂቃ በመግባት ስታሸንፍ፥ጸሀይ ገመቹ 1 ሰዓት ከ5 ደቂቃ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛ ርቀቱን ጨረሳለች፡፡

አውስትራሊያ በተደረገ የግማሽ ማራቶን የሴቶች ውድድር እንዲሁ በቀለች ጉደታ 1 ሰዓት ከ8 ደቂቃ በመግባት ስታሸንፍ በወንዶች ኪሮስ አሸናፊ 1 ሰዓት ከ5 ደቂቃ በመግባት 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል፡፡

በተጨማሪም በሜክሲኮ የሴቶች ማራቶን አማኔ በሪሶ 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ በመግባት ቀዳሚ ስትሆን ሙሉየ ደቀቦ ደግሞ 2 ሰዓት ከ31 ደቂቃ በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.