የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 20 ይጀመራል
አበባ ፣ ነሐሴ 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 20 እንደሚጀምር ተገለፀ፡፡
የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ1ኛ ዙር መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል፡፡
በዚህም የፊፋና ካፍ የውድድር ሰሌዳዎችን በማየት፣ ለውድድር ዝግጁ የሆኑ ስታድየሞችን በመገምገም እና የሊጉን ስፖንሰር አስተያየት ተካቶ በመዘጋጀት ለፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ክለቦች መላኩ ተገልጿል፡፡
መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም የሚጀምረው ውድድር ለአምስት ሳምንታት በባህር ዳር ቆይታ ካደረገ በኋላ ከ6ኛ እስከ 10ኛ ሳምንት በድሬደዋ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡
እንዲሁም ከ11ኛ እስከ 15ኛ ሳምንት ያለው ውድድር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡
የሁለተኛው ዙር የሊጉ ውድድር መርሃ ግብርም የስታዲየሞች ሁኔታ ከተገመገመ በኋላ በቀጣይ ለክለቦች እንደሚገለፅ መጠቆሙን ከሊግ ኩባንያው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡