Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የቴሌኮም ኅብረት ጋር ያላትን ትብብር እንደምታጠናክር ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የቴሌኮም ኅብረት ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ዘነበ ከበደ ተናገሩ፡፡

የዓለም አቀፉ የቴሌኮም ኅብረት በሮማኒያ ቡካሬስት ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ÷ ድርጅቱን በቴሌኮሙኒኬሽን ልማት ቢሮ ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የነበሩትን ዶረን ቦግዳንን ዋና ጸሐፊ አድርጎ መርጧል።

አምባሳደር ዘነበ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ በቴሌኮም ልማት ዘርፍ፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በዘርፉ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እየሠራቻቸው ያሉ ሥራዎችን አብራርተዋል፡፡

በቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ላይ ያተኮረ የአገር ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው ገልጸው÷ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የቴሌኮም ኅብረት ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ፀድቆ ወደ ሥራ መግባቱ፣ የቴሌኮም ዘርፉን በከፊል ወደ ግል የማዞር ሥራዎች እና ምቹ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር በትኩረት እየተሠራ ነው ማለታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.