Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር ከተማ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተቋቋመው የማንጎ ጭማቂ ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኤ ስኩየር ኤ” በተባለ ድርጅ ት የተቋቋመው “ስላይስ” የማንጎ ጭማቂ ፋብሪካ ዛሬ በባህርዳር ከተማ ተመርቋል፡፡

ፋብሪካው ከ200 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተቋቋመ ሲሆን በቀን 112 ሺህ ሊትር እንዲሁም በዓመት ደግሞ 33 ሚሊየን 600 ሺህ ሊትር ጭማቂ የማምረት አቅም እንዳለው ተገልጿል፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ እንዳለው መኮንን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር መሰል ፋብሪካዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል።

አክለውም መንግስት በሀገር በቀል ኢኮኖሚ የተቃኘ ፖሊሲ ቀርጾ የግሉ ዘርፍ እንዲነቃቃና ተሳታፊ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የ”ኤ ስኩየር ኤ” ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አምሃ መልካሙ በበኩላቸው ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ፥ ለ1 ሺህ 900 ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

ለፋብሪካው የሚሆን ግብዓት ለማግኘትም ከበርካታ አርሶ አደሮች ጋር ቀጥተኛ የምርት ገበያ ትሥሥር በመፍጠር ግብርናውን ለማበረታታት ይሠራል ነው የተባለው።

በአማራ ክልል 3 ሺህ 442 ኢንዱስትሪዎች በአራት ዘርፎች በመሰማራት ከ39 ሺህ ለሚልቁ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠራቸውተጠቁሟል፡፡

በዓለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.