Fana: At a Speed of Life!

ዩኔስኮ ለኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሣይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራና ለማህበረሰብ ሬዲዮ አቅም ግንባታ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ከዩኔስኮ የተግባቦትና መረጃ ረዳት ዳይሬክተር ቶፊቅ ጀላሲ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ዶክተር በለጠ ሞላ÷ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዲጂታልትራንስፎርሜሽን ሥራ እና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የወደሙ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢዎችን መልሶ የመገንባት ሥራን ዩኔስኮ እንዲደግፍ ጠይቀዋል።

በተለይ የማህበረሰብ ሬዲዮዎቹ በጦርነቱ ምክንያት የስነ ልቦና ጫና የደረሰባቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ለማገዝ ጉልህ ጠቀሜታ ያላቸው በመሆኑ ድጋሚ የመጠገንና የአቅም ግንባታ ስራ እንደሚያስፈልጋቸው መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ዶክተር ቶፊቅ ጀላሲ÷ ዩኔስኮ የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራ እና የማህበረሰብ ሬዲዮ መጠገንና አቅም ግንባታ ላይ አስፋላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

በተመሳሳይ ዶክተር በለጠ ከቱርክ የትራንስፖርትና መሰረተ ልማት ምክትል ሚኒስትር ኦመር ፋታህ ጋር በሣይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በጋራ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በመረጃ መረብ ደኅንነት፣ በዓቅም ግንባታ፣ በቴሌኮም ዘርፍ፣ በሳተላይት ቴክኖሎጂ እንዲሁም የቱርክ የቴክኖሎጂ ካምፓኒዎች በኢትዮጵያ መሰማራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.