Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያና በሕንድ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንሠራለን- በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና በሕንድ መካከል ያለውን ግንኙነት በትምህርትና በኢንቨስትመንት ለማጠናከር እንደሚሠሩ በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር ሼሪ ሮበርት ሸክቲንግተን ገለጹ፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ በኢትዮጵያ ከሕንድ አምባሳደር ሼሪ ሮበርት ሸክቲንግተን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ዶክተር ፍጹም በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ የሀገራቱን ግንኙነት በትምህርትና ምርምር፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና በባህል ግንኙነቶች ማጠናከር ይገባል፡፡

በተለይም ሕንድ በማኅበራዊ፣ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ለኢትዮጵያ ለምታደርገው ድጋፍ ማመስገናቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ሼሪ ሮበርት ሸክቲንግተን በበኩላቸው÷ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተጀመሩ የኢንቨስትመንትና ሁሉን አቀፍ ግንኙነቶች የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.