Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ለገና በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ለገና በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

የፅህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ነጋ ይስማው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ የገና በዓልን ተከትሎ የእርድ እንስሳት አቅርቦት እጥረት በገበያው እንዳይፈጠር ቀድሞ የዝግጅት ስራው ተጀምሯል፡፡

የፅህፈት ቤቱ ዝግጅትም ከ15 ቀናት በፊት መጠናቀቁን ገልፀው ፥ በክልሉ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት እንዳለም ነው የተናገሩት።

የስጋ ምርት ፍላጎትን መሰረት በማድረግም የበሬ፣ በግ፣ ፍየልና የዶሮ ውጤቶችን በበቂ ሁኔታ ማዘጋጀት መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

ከክልሉ አልፎ ወደ መሀል ሀገርና የተለያዩ አካባቢዎች የእርድ እንስሳት እየቀረበ እንዳለ የተገለፀ ሲሆን÷ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ለማድረግ ገበያ የማረጋጋት ስራው ከክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ጋር እየተከናወነ ነው ተብሏል።

በምናለ አየነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.