ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር በኮቪድ-19 ርምጃዎች ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር በኮቪድ-19 እርምጃዎች ላይ ተወያዩ።
በመድረኩ የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ እና መንግሥት የሚወስዳቸውን ተጨማሪ ርምጃዎች በተመለከተ ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከሰዓት በኋላም ከሁለተኛው ቡድን የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ወቅትም የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች የኮቪድ-19 ተጽዕኖ ለመቀነስ እና መንግሥት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ለመደገፍ ስላሳዩት መልካም ፈቃድ አመሰግነዋል።
በዚህ ፈታኝ ጊዜ እና በሌሎችም ጊዜያት እንዲህ ያለው የትብብር መንፈስ ለዜጎች የሚጠቅመውን ለማድረግና ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ጎዳና ለመውሰድ እንደሚያስችል አስታውቀዋል።