Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት 6 ወራት 42 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ሥድስት ወራት 42 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ያለፉት ስድስት ወራትን የስራ አፈጻጸም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ገምግሟል፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ÷ የከተማ አስተዳደሩ ለሚፈልጋቸው ለልማት ለመልካም አስተዳደር እና ለልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ የሚውል በጅት ለመሰብሰብ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተዋል፡፡

በዚህ መሰረትም ቢሮው በ2015 በጀት ዓመት 70 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ባለፉት ስድስት ወራትም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ 39 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 42 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

በዚህም የአቅዱን 107 በመቶ ማሳካቱን መቻሉን ጠቁመው ÷ ካባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻርም የ10 ነጥብ 2 በሊየን ብር ብልጫ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡

ለተገኘው ስኬትም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተጀመረው ንቅናቄ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን አውስተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለግብር ከፋዮች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ቀልጣፋ እና ፍትሃዊ እንዲሁም ተደራሽ አገልግሎት መስጠት መቻሉ ለስኬቱ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቁመዋል፡፡

ከሌብነት ጋር ተያይዞም የስነ ምግባር ችግር ያለባቸውን ባለሙያዎች እና ግብር ከፋዮች በጥናት ላይ የተመሰረታ ሕጋዊና አስተዳደራዊ ርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።

ሀሰተኛ ደረሰኝ መስጠት ፣ ያለደረሰኝ አገልግሎትና ዕቃ መሸጥ ፣ ከዋጋ አሳንስ መሸጥ ባለፉት ስድስት ወራት የተስተዋሉ ተግዳሮቶች መሆናቸውንም አስታውሰዋል፡፡

ያለንግድ ፈቃድ እየሰሩ ግብር የማይከፍሉ ዜጎችንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ወደ ታክስ ስርዓት እንደሚገቡ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.