Fana: At a Speed of Life!

በሩሲያ-ዩክሬን ጉዳይ ላይ የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ ያለስምምነት ተቋጨ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ-ዩክሬን ጉዳይ ላይ ለሁለት ቀናት በሕንድ ቤንጋሉሩ የመከረው የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ ያለስምምነት ተጠናቀቀ፡፡

የቡድን 20 አባል ሀገራቱን በሊቀ መንበርነት የምትመራው ሕንድ ጉዳዩ ለውይይት እንዲቀርብ ፍላጎት ባታሳይም÷ በምዕራባውያን ሀገራት ጉትጎታ እንደተወያዩበት ተገልጿል፡፡

ውይይቱን ተከትሎም ÷ “ሞስኮ ኪየቭ ላይ ጥቃት ፈጽማለች” ተብሎ በወጣው የአቋም መግለጫ ላይ ቻይና ሳትፈርም መቅረቷን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ባለፈው ሕዳር ወር በዚሁ ጉዳይ በኢንዶኔዢያ ባሊ የመከረው የቡድን 20 አባል ሀገራቱ ስብሰባ በሐሳብ ልዩነት መበተኑ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.