Fana: At a Speed of Life!

የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የዓለም ባንክ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የተወዳዳሪነት አቅምን ለማሳደግ የዓለም ባንክ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለፀ፡፡

በዓለም ባንክ ድጋፍ ባለፉት ስምንት ዓመታት በቦሌ ለሚ ሁለት እና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ሲተገበር የቆየው የተወዳዳሪነትና የስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጀክት መዝጊያ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ፕሮጀክቱ በቦሌ ለሚ ሁለት እና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ከ10ሺ በላይ ለሚሆኑ ወጣት ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር  እና  የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በማሳደግ በኩል አዎንታዊ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ እና በውጤቱም የሀገርን እድገትና ልማት እንዲደግፍ ለማድረግ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ  ላበረከቱ  ኃላፊዎች፣ ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት  ምስጋና  ማቅረባቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዓለም ባንክ ባደረገው የ425 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ በቦሌ ለሚ ሁለት እና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ማከናወን የተቻለ ሲሆን ከ10 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.