Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአመታዊ “ሰካይትራክስ ውድድር” በ5 ዘርፎች አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአመታዊው “ሰካይትራክስ ውድድር” በአምስት ዘርፎች በማሸነፍ ሽልማት ተቀዳጅቷል፡፡

በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው የ2023 ስካይትራክስ የአየር መንገዶች ሽልማት ስነስርዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአምስት የተለያዩ ዘርፎች የክብር ሽልማቶችን አግኝቷል።

በዚህም አየር መንገዱ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድን ለስድስተኛ ጊዜ፣ በምርጥ ቢዝነስ ካላስ አየር መንገድ ዘርፍ እና በምርጥ ኢኮኖሚ ክላስ አየር መንገድ ዘርፍ ለአምስተኛ ጊዜ ሽልማት ማግኘቱ ተገልጿል።

እንዲሁም ለተከታታይ 2ኛ ጊዜ ፅዱ የአፍሪካ አየር መንገድ ዘርፍ ሽልማት እና ምርጥ የቢዝነስ ክላስ የምግብ እና የመጠጥ መስተንግዶ አገልግሎት ዘርፍ ሽልማት ማግኘቱን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.