Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ክልል ገቢዎች ቢሮ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ገቢዎች ቢሮ ባለፉት 11 ወራት ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ቢሮው ባለፉት 11 ወራት ከ3 ቢሊየን 195 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

የቢሮው ኃላፊ አወል አብዱ ለአፋር ክልል መገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት÷ ከ3 ቢሊየን 104 ሚሊየን 422 ሺህ ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡

አፈጻጸሙ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 48 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.