Fana: At a Speed of Life!

አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አክሲዮን ማህበር ወደ ባንክነት ተሸጋገረ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር “ስኬት ባንክ አክሲዮን ማህበር” በሚል ስያሜ ወደ ባንክነት ተሸጋግሯል፡፡

የብድርና ቁጠባ ተቋሙ “ስኬት ባንክ አክሲዮን ማህበር” በሚል ስያሜ የባንክ አገልግሎት ለመጀመር የሽግግር ማብሰሪያ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ተቋሙ 26 ባለአክሲዮኖች እና 10 ቢሊየን ብር የተፈረመ ካፒታል ይዞ ወደባንክ ለማደግ ሽግግር መጀመሩ ተመላክቷል፡፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.