Fana: At a Speed of Life!

ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች 3 ነጥብ 64 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች 3 ነጥብ 64 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃጸሙን አስመልክቶ ከላኪዎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የግምገማ መድረክ እያካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ፣ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ፣ የወጪ ምርት ላኪ ባለሀብቶች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በ2015 በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች 5 ነጥብ 21 ቢለየን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 3 ነጥብ 64 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን አቶ ካሳሁን ጎፌ ገልጸዋል።

ውጫዊ እና ተቋማዊ የውስጥ ችግሮች የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት አላስቻሉም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከላኪዎች ጋር እየተደረገ ያለው የአፈፃጸም ግምገማ የምክክር መድረክም በስራ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመፍታት ከወጪ ንግድ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ሚኒስቴሩም በ2016 በጀት ዓመት የወጪ ምርቶች በጥራት እና መጠን ለውጭ ገበያ የሚቀርቡበትን ስርዓት በማሻሻል ላኪዎች የሚያጋጥማቸውን ችግር መፍትሔ ለመስጠት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አመላክተዋል።

ህገ-ወጥ ንግድ፣ ኮንትሮባንድ፣ በንግድ ፈቃድ ሽፋን ህገ-ወጥነት መስፋፋት፣ ተደራራቢ የታክስ ክፍያ መኖር፣ ከጉምሩክ ኮሚሽን እውቅና ውጭ አላስፈላጊ ኬላዎች መብዛት እና ሌሎች ችግሮች ለወጪ ንግድ አፈፃጸም ጉድለት አሉታዊ ጫና እያሳደሩ መሆናቸው በውይይቱ ተነስቷል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.