Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ሁለት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ሁለት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስተር አስታወቀ።

በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 2 ሺህ 650 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ነው የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱዩት ባወጡት መግለጫ ያስታወቁት።

በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 263 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሁለቱም ወንድ ኢትዮጵያዊያን እድሜያቸው 24 እና 33 ዓመት የሆኑ ናቸው።
ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው አንደኛው የትግራይ ክልል ነዋሪና የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ ሲሆን ሁለተኛው ከሶማሌ ክልል (ጂግጅጋ ለይቶ ማቆያ) ነው።

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 2 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 108 መድረሱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱዩት ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.