Fana: At a Speed of Life!

የወርቅ ግብይት ሥርዓትን የሚያዛቡ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ እንሠራለን- ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባልተገባ መንገድ የወርቅ ግብይት ሥርዓትን የሚያዛቡ አካላትን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እንደሚሠሩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የተመራ ልዑክ በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ጋቢሳ ቀበሌ የካሩት ማይኒግ ወርቅ አምራች ማኅበር የሥራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡

ብዝሃ ክፍለ-ኢኮኖሚ ላይ በማተኮር ዜጎች በተለያዩ ዘርፎች የኢኮኖሚ ዐቅማቸውን እንዲያሳድጉ ብልጽግና ፓርቲ እየሠራ መሆኑን ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡

የወርቅ ማዕድን ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር የላቀ ሚና ቢኖረውም÷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያሉ ክፍተቶችን በመጠቀም የዘራፊዎች ሲሳይ ሆኗል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ይህንን ችግር በመቅረፍ የሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት አምራች ማኅበራት በተሻለ ጥራት ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ እንዲያቀርቡ እንሠራለን ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡

በዘርፉ የሚስተዋሉትን ችግሮች በአፋጣኝ ለመፍታት ሥራዎች መጀመራቸውንም ነው ያነሱት፡፡

በወርቅ አምራቾች አካባቢ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የክልሉ መንግሥት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል፡፡

ባልተገባ መንገድ የወርቅ ግብይትና ሥርዓትን የሚያዛቡ አካላት የሕግ ተጠያቂነት እንዲኖርም ይሰራል ብለዋል።

አምራቾች ከሊዝ ማሽን ጋር በተያያዘ የሚያነሷቸው የአቅርቦት ችግሮች እንዲፈቱም ከልማት ባንክ ጋር በማስተሳሰር ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሠሩ ነው የገለጹት፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.