Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ6 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ላስመዘገቡ ባለሐብቶች ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው ስድስት ወር 6 ነጥብ 857 ቢሊየን ብር ሐብት ላስመዘገቡ ባለሐብቶች ፈቃድ መስጠቱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ፈቃድ የተሠጠባቸው ዘርፎችም ግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና አገልግሎት መሆናቸውን የቢሮው ኃላፊ አባስ መሐመድ (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በግብርና ለ68፣ በኢንዱስትሪ ለ44፣ በአገልግሎት ለ20 በድምሩ ለ132 ባለሐብቶች ፈቃድ መሰጠቱንም ነው የገለጹት፡፡

ፈቃድ የተሰጠባቸው ፕሮጀክቶችም ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገቡ÷ 9 ሺህ 294 ቋሚ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም 13 ሺህ 742 ጊዜያዊ የሥራ ዕድ እንደሚፈጥሩ አመላክተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.