Fana: At a Speed of Life!

የዘንድሮ የተፋሰስ ልማት ሥራ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በዘንድሮ የበጋ ወቅት የሚካሄደው የተፋሰስ ልማት ሥራ መርሃ ግብር በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ተጀምሯል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሐብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምሕረት÷ በዚህ ዓመት ከ9 ሺህ 60 በላይ ተፋሰሶች እንደሚለሙ ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ከ376 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን በዋና ዋና ሥራዎች ለማልማት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ የተፋሰስ ልማት ሥራዎቹን ውጤታማ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ እየሠሩ መሆናቸውንም አስገንዝበዋል፡፡

ለሥራው መሳለጥ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች የተሟሉ መሆናቸውን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ ከ3 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ የሥራ መሳሪያዎች ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡

በቀጣይ በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች የተፋሰስ ልማት ሥራዎቹ እንደሚጀመሩ ነው የተገለጸው፡፡

ባለፉት ዓመታት በተሠራ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሐብት ልማት ሥራዎች ከ19 ሺህ በላይ ተፋሰሶች መልማታቸው ተጠቁሟል፡፡

በዘንድሮው ለ25 ቀናት በሚቆየው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሕዝብ እንደሚሳተፍ ይጠበቃል፡፡

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.