Fana: At a Speed of Life!

ሹመቱ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሲመክሩበት ቆይተው የወሰኑት መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት የተሰጠው ሹመት የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሲመክሩበት ቆይተው የወሰኑት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ሹመቶችን ባጸደቀበት ወቅት ነው፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ፓርቲው ከበርካታ እጩዎች ውስጥ ባላቸው ልምድ ኢትዮጵያን ማገልገል የሚችሉ እጩዎችን ወደ ፊት ለማምጣት የወሰነበት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በተለይም ከተሿሚዎች ውስጥ ሁለቱ ከብልጽግና ፓርቲ አባል ውጪ መሆናቸው ለኢትዮጵያ ቅድሚያ የተሰጠበት እና ልምድ እና እውቀት ብቻ መስፈርት የሆነበት መሆኑን አውስተዋል፡፡

ከየትኛውም ፓርቲ ቢሆን ልምድና እውቀት ያላቸውን ወደፊት ማምጣቱ እንደሚቀጥልም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ባለው የመተካካት ባህል የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሥራ አስፈፃሚነታቸው በክብር መሸኘታቸውን ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው እንዲሾሙ የቀረበለትን ሹመት መርምሮ አጽድቋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.