Fana: At a Speed of Life!

የቅርፅና የአገልግሎት ማሻሻያ የተደረገባቸው የኖኪያ ስልክ ቀፎች ገበያ ላይ ሊውሉ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤች ኤም ዲ ኩባንያ የቅርጽና የአገልግሎት ማሻሻያ የተደረገባቸው አዳዲስ የኖኪያ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ለገበያ ሊያቀርን እንደሆነ አስታወቀ፡፡

ኩባንያው እንዳስታወቀው÷ የስልክ ቀፎዎቹ የነበራቸውን መለያ ሳይለቁ የተወሰነ የቅርፅ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ማስተካከያ ተደርጎባቸው በአዲስ መልክ ለገበያ ይቀርባሉ፡፡

እነዚህን አዳዲስ ምርቶች ተከትሎ ከዚህ በፊት ገበያ ላይ ሲቀርቡ የነበሩት የኖኪያ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ከገበያ ላይ ሊጠፉ እንደሚችሉ ነው የተገለፀው፡፡

በፊንላንዱ ሁለገብ የስልክ ቀፎ አምራች ኤች ኤም ዲ ኩባንያ የሚመረቱት የኖኪያ ሞባይል ስልኮች በፈረንጆቹ 2011 በአውሮፓ ገበያ ቀዳሚውን ስፍራ ይዘው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የኖኪያ ስልኮች በዘመናዊ ስልኮች በመተካታቸው ምክንያት ኖኪያ በ2014 ከስልክ ሽያጭ ገበያ ወጥቶ እንደነበር ተመላክቷል፡፡

የኤች ኤም ዲ ኩባንያ በገጠመው የገበያ ችግር ምክንያትም በፈረንጆቹ 2013 የኖኪያ ስልክ አምራች ክፍሉን ለማይክሮሶፍት ኩባንያ በ5 ነጥብ 4 ቢሊየን ዩሮ መሸጡን አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.