Fana: At a Speed of Life!

የሥርዓተ ትምህርት ማሻሻያው ተማሪዎች ሙያዊ ክህሎት እንዲኖራቸው የሚያስችል ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሥርዓተ ትምህርት ማሻሻያ ተማሪዎች ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር ሙያዊ ክህሎት እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ÷ የትምህርት ሥርዓቱን ማሻሻያና እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ፋይዳ በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ÷ በሥርዓተ ትምህርቱ ላይ የተደረገው ማሻሻያ ተማሪዎች ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር ክህሎት እንዲኖራቸው የሚያስችል እንደሆነም ነው የተናገሩት።

በሥርዓተ ትምህርቱ የተደረገው ማሻሻያ ተማሪዎች እንደየተሰጥኦዋቸው በአይሲቲ፣ በእርሻ፣ በኪነጥበብና መሰል የትምህርት መስኮች የዳበረ ሙያዊ ክህሎት እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

ሥርዓተ ትምህርቱን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ባይቻልም በሙከራ ደረጃ ስኬታማ እንደሆነም ነው ያነሱት።

በቀጣይም ሁሉንም ዓይነት የትምህርት ዓይነቶች በተሟላ ሁኔታ ማስጀመር የሚያስችል የመጽሓፍት ሕትመት ይደረጋል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

የበጀት እጥረት የመጽሓፍት ህትመቱ ላይ እንቅፋት እየፈጠረ ቢሆንም በተለያየ መንገድ የመጽሓፍት ሕትመቱን ለማከናወን እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል ሚኒስትሩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.