Fana: At a Speed of Life!

ለሊዝ ፋይናንስ ተጠቃሚዎች ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ተላልፏል-የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ለሊዝ ፋይናንስ ተጠቃሚዎች ከ10 ቢሊየን ብር በላይ መተላለፉን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በማእድን ዘርፍ ለተሰማሩ 14 ኤክስካቫተር፣ በቱሪዝም ዘርፍ ለተሰማሩ 28 የቱር ኦፐሬተር መኪኖች እና ለኮንስትራክሽን ስራ የሚሆኑ ሰባት ሎደሮች ለደንበኞቹ በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ማቅረቡን ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው(ዶ/ር)÷ በርክክቡ ላይ ባደረጉት ንግግር የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ከፍተኛ እድገት እያሳ ነው ብለዋል።

በቱሪዝም፣ በኮንስትራክሽን እንዲሁም በማዕድን ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ዜጎች የሚያደርገው ድጋፍ በየጊዜው እያደገ መሆኑንም አንስተዋል።

ከአራት አመታት በፊት ይሰጥ የነበረው 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር እንደነበር አስታውሰው ዘንድሮ በስድስት ወራት 10 ቢሊየን ብር መሰጠቱን ተናግረዋል።

የሊዝ ፋይናንሲንግ በብድር አመላለሱም በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው የተላለፉት ማሽነሪዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖራቸው ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም የተበላሸ ብድር መጠን 36 በመቶ እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ ወደ 1 ነጥብ 6 በመቶ ወርዷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.