Fana: At a Speed of Life!

ዋና ዋና የሳይበር ጥቃት ዓይነቶች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም በይነመረብ ላይ ያኖሩትን መረጃ በመበርበር ጥቃት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡

የሳይበር ጥቃቶች በተለየ በሀገር ደረጃ መዋቅራዊ ጉዳቶችን ያስከትላል።

እነዚህ የሳይበር ጥቃቶች በተለያዩ የማጥቂያ መንገዶች የሚፈጸሙ ሲሆን ፥ በሳይበር ምህዳሩ በስፋት የተለመዱ የሳይበር ጥቃት ዓይነቶች የሚከተሉት ናቸዉ፡-

1. የአገልግሎት መቋረጥ :- ይህ የሳይበር ጥቃት ዓይነት የሲስተሞችን አቅም ባልተፈለገ ሁኔታ በማጨናነቅ የህጋዊ ተጠቃሚው አገልግሎት አሰጣጥ በማቋረጥ የሚፈጸም ጥቃት ነው ፡፡

2. የድረ ገጽ የዲፌስምነት ጥቃት (መልክን የመቀየር ጥቃት )፡- የተጠቂውን ድረ- ገጽ በሀሰተኛ ሰነዶች በመቀየር የሚፈጸም የጥቃት ዓይነት ነው ፡፡

3. የማልዌር ጥቃት ፡- ሆን ተብሎ እና ሳይጠበቅ ጣልቃ በመግባት መደበኛ የኮምፒውተር ተግባርን የሚያውክ የጥቃት ዓይነት ነው፡፡

4. ስፓም :- ብዛት ያለውና የአጥፊነት ተልእኮ ያላቸው ኢሜሎችን በመላክ የሚፈጸም የጥቃት ዓይነት መሆኑን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

5. የፌሺንግ ጥቃቶች ፡- የሳይበር ጥቃት የተለያዩ የማታለያ እና የማዘናጊያ ዘዴዎችን በመጠቀም አጭበርባሪዎች ከተጠቃሚዎች ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን ለመመዝበር የሚደረግ የማህበራዊ ምህንድስና ጥቃት ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.