Fana: At a Speed of Life!

ምባፔ በክረምት የዝውውር መስኮት ማድሪድን ለመቀላቀል ተስማማ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓሪሴንት ዥርሜይ አጥቂ ኪሊያን ምባፔ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል ተስማምቷል፡፡

የ25 ዓመቱ ፈረንሳዊ ምባፔ÷ ሪያል ማድሪድ እና ፒ ኤስ ጂ በሻምፒዮንስ ሊጉ የማይገኛኙ ከሆነ በቅርቡ ለማድሪድ የኮንትራት ፊርማውን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡

ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫን ማሸነፍ የቻለው ወጣቱ አጥቂ በፈረንሳዩ ክለብ ፓሪሴንት ዥርሜይ 244 ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡

በመጪው ሰኔ ወር ከፒ ኤስ ጂ ጋር ያለው ኮንትራት የሚጠናቀቀው ምባፔ ቀደም ሲል ክለቡን እንደሚለቅ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.