Fana: At a Speed of Life!

አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በኢትዮጵያ ለ48ኛ ጊዜ ይከበራል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን “ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ቀኑ በኢትዮጵያ ለ48ኛ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ113ኛ ጊዜ ይከበራል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋየ (ዶ/ር) የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ÷የሴቶችን ቀን የምናከብረው ሴቶች እኩልነትን ከማስከበር እስከ ሀገረ መንግስት ምስረታ ድረስ ያደረጓቸውን ተጋድሎዎች በማስታወስ ነው ብለዋል።

ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች በማቋቋም፣ብድሮችን በማመቻቸትና የስራ እድል በመፍጠር ሚኒስቴሩ እየሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በተሰራው የንቅናቄ ስራም በአይነትና በገንዘብ ድጋፍ እንደተገኘና በቀጣይም የንቅናቄ ስራው ተጠናክሮ አንደሚቀጥል ተነስቷል፡፡

በተጨማሪም÷በገጠር የሚገኙ ሴቶች የታዳሽ ሀይል ተጠቃሚ ማድረግ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ በሚደረጉ ውይይቶች ሴቶችን ተሳታፊ በማድረግ እንዲሁም በጤና እና በኢኮኖሚ ብቁ የሆኑ ሴቶችን ለመፍጠር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነውም ተብሏል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በዓሉ ከየካቲት 1 እስከ መጋቢት 18 ከፌደራል ጀምሮ እስከ ታችኛው የወረዳ መዋቅር ድረስ በቅንጅትና በትብብር እንደሚከበርም እርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

በትዕግስት አስማማው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.