Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ130 ሺህ ሔክታር በላይ በበጋ መስኖ ስንዴ እየለማ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ130 ሺህ 392 ሔክታር በላይ በበጋ መስኖ ስንዴ እየለማ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

170 ሺህ 199 ኩንታል ማዳበሪያና 172 ሺህ 794 ኩንታል ምርጥ ዘር ጥቅም ላይ መዋሉም ተገልጿል፡፡

በበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱ ከ426 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡

በድርቅ፣ በግጭት፣ በበረሃ አንበጣ፣ በግሪሳ ወፍ እና መሰል ምክንያቶች የታጣውን ምርት ለማካካስም በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.