Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የመግባቢያ ስምምነት ዓለም አቀፍ ሕጋዊነት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደራል ፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የተዘጋጀው በኢትዮጵያና ሶማሊላንድ መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ዓለም አቀፍ ሕጋዊነት እና አንድምታ ላይ ያተኮረ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው።

በመድረኩ÷ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አበባ እምቢአለ፣ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፌ ቡላ፣ የፍትሕ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

አምባሳደር ደግፌ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር÷ ተቋሙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የሀገርን ጥቅም በሚያስከብሩ ጉዳዮች ላይ ጥናት እንደሚያደርግና የግንዛቤ ማስጨበጫ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

የመድረኩ ዓላማም ስምምነቱ ያለውን ዓለም አቀፋዊ ሕጋዊነት እና አንድምታ ማስጨበጥ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ሕጋዊነት እና አንድምታ ላይ ያተኮረ የውይይት መነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ መሆኑም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.