Fana: At a Speed of Life!

በ180 ሚሊየን ዶላር የሚተገበር የግብርና ዘርፍ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርናውን ዘርፍ ይደግፋል የተባለ በ180 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚተገበር ፕሮጀክት በግብርና ሚኒስቴር  ይፋ ሆነ፡፡

ፕሮጀክቱ በተለያዩ አጋር አካላት አማካኝነት የሚተገበር መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ  ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)÷ ፕሮጀክቱ በሲዳማ፣ በኦሮሚያ፣ ትግራይ ፣ሶማሌና አፋር ክልሎች ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን  ገልጸዋል፡፡

በእነዚህ ክልሎች ያለውን የድርቅ ሁኔታ በመዋጋት በመስኖ ልማት ውጤታማ መሆኑ እንዲቻል፤ አርሶአደርም ከሚሰሩት ፕሮጀክቶች እንዲጠቀም መንግስት በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት፡፡

በዚህ ፕሮጀክት በተፈጥሮ የሚገኝ ውሃን ወይም  የከርሰ ምድር ውሃን በመጠቀም  የመስኖ ልማት አውታሮችን በመገንባት አርሶአደሩ በቀላሉ በዓመት ሦስትና ከዚያ በላይ  ጊዜ እንዲያመርት ለማስቻል ይሰራል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዉሃ ሀብትን ተጠቅሞ  ብዙ ምርት ማምረት እቅዷን ለማሳካት እና በምግብ እራሷን ለመቻል የምታደርገው ጥረት ውጤት እንዲያመጣ መሰል ፕሮጀክቶች የላቀ ድርሻ እንዳላቸውም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የተጀመረው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ  እዉን እንዲሆን እንደሚያግዝም  ተመላክቷል።

በጥላሁን ይልማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.