Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሚኒስቴር ከዩጋንዳ አቻው ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ከዩጋንዳ መከላከያ ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

የዩጋንዳ መከላከያ ሚኒስትር ቪሴንት ባሙላንጋኪ ሴምፒጅ እና የሀገሪቱ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ዊልሰን ዕምባሱ ዕምባዲ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የስራ ሃላፊዎቹ የመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ሲደርሱ የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሀም በላይ (ዶ/ር፣ የጦር ሀይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ እና ሌሎች ጄኔራል መኮንኖች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሁለቱ አገራት መከላከያ ሚኒስትሮች የሁለትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረሙ ሲሆን÷የየሀገራቱ ኢታማዦር ሹሞችም የመግባቢያ ሰነዱን ለማስፈፀም በሚያስችል ዝርዝር ዕቅድ በያዘ ሰነድ ላይ ተፈራርመዋል።

አብርሀም በላይ (ዶ/ር)÷ ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክ ገልፀው በመረጃ ልውውጥ፣ በወታደራዊ አቅም ግንባታ፣ በቀጠናዊ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት መፈራረማቸውን ተናግረዋል።

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በበኩላቸው÷ከዩጋንዳው ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ዊልሰን ዕምባሱ ዕምባዲ ጋር የተደረሱ ዝርዝር ወታደራዊ ስምምነቶችን ወደ ተግባር ለመቀየር በትኩረት እንሰራለን ብለዋል፡፡

የዩጋንዳ መከላከያ ሚኒስትር ቪሴንት ባሙላንጋኪ ሴምፒጅ÷ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበው ለስምምነቱ ተግባራዊነት ቁርጠኛ ነን ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.