ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በኬኒያ የአይሲቲ ፓርክን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በኬኒያ ናይሮቢ የወጣቶችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተሳትፎ የሚያሳይ የአይሲቲ ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለሁለት ቀናት ጉብኝት ኬኒያ ናይሮቢ የገቡ ሲሆን÷በጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ጣቢያ በኬኒያው ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በመቀጠልም ፕሬዚዳንት ሩቶ የወጣቶችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተሳትፎ የሚያሳይ የአይሲቲ ፓርክ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) አስጎብኝተዋል።