Fana: At a Speed of Life!

ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የኦዲት ሪፖርትና ዕቅድ በወቅቱና በጥራት አያቀርቡም ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የኦዲት ሪፖርት እና ዕቅድ በወቅቱና በጥራት እንደማያቀርቡ የገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
 
የሚኒስቴሩ የስድስት ወራት የኢንስፔክሽን አፈጻጸምን አስመልክቶ ከፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የውስጥ ኦዲት እና የፋይናንስ ኃላፊዎች ጋር ምክክር አድርጓል።
 
በምክክር መድረኩም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ማቅረብ የሚገባቸውን የኦዲት ሪፖርት እና ዕቅድ በወቅቱና በጥራት እንደማያቀርቡ ገልጿል፡፡
 
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ተቀባይነት የሌላቸውን ምክንያቶች በመፍጠር የኦዲት ሪፖርትና ዕቅዳቸውን በወቅቱና በጥራት ባለማቅረባቸው ትልቅ ክፍተት ተፈጥሯል።
 
ስራን አቅዶ ያለመስራትና በተገቢው መንገድ ሪፖርት ያለማድረግ አሰራር ሊቀጥል አይገባም ሲሉም አበክረው አሳስበዋል፡፡
 
የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደርን ዲጂታል ማድረግ አንዱ የትኩረት አቅጣጫ በመሆኑ ከወረቀት ስራ ተላቅቆ ዕቅድና ሪፖርትን በዲጂታል ስርዓት ማከናወን እንደሚገባም ማስገንዘባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ለዚህ መሰረተ ልማት ዝርጋታም ሚኒስቴሩ ተገቢውን የበጀት ድጋፍ እንደሚያደርግ ሚኒስትር ዴኤታው አረጋግጠዋል።
 
የኦዲት ሪፖርት አቀራረብ በሚኒስቴሩ የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስራ አስፈጻሚ በኩል የተቀናጀ የሪፖርት አስተዳደር ስርዓት በሚል ስያሜ በተዘረጋው ዲጂታል ስርዓት በኩል ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.