Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የእንስሳት ልማትና የልህቀት ማዕከል ፕሮጀክትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የእንስሳት ልማት እና የልህቀት ማዕከል ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ ከተማችንን ወደ አምራችነት በማሸጋገርና የምርት አቅርቦትን በማሻሻል የገበያ መረጋጋት ከፈጠርንባቸው ስራዎቻችን መካከል አንዱ የእንስሳት ልማት እና የልህቀት ማዕከል ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡

በ14 ሔክታር መሬት ላይ የተገነባው ፕሮጀክቱ ለከተማዋ ነዋሪዎች ጥራት ያላቸውን የእንስሳት ምርቶች እያቀረበ እንደሚገኝ ገልፀው፤ ማዕከሉ ለበርካቶች የስራ እድል የፈጠረና የአካባቢውን አርሶ አደሮች የቴክኖሎጂ ሽግግር ተጠቃሚ እያደረገ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.