Fana: At a Speed of Life!

የረመዳን ወር ነገ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ 1445ኛው የረመዳን ወር ነገ እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የረመዳን ወር ነገ ሰኞ እንደሚጀምር ታውቋል፡፡

ታላቁን የረመዳን ወር በመተሳሰብና አላህን በመለመን ማሳለፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ መግለጻቸው ይታወሳል።

ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የረመዳን ወርን አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ በሰጡት መግለጫ÷የምንቀበለው የረመዳን ወር የእዝነት፣ የምህረትና ከእሳት ነጃ የምንወጣበት፣ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው የዒባዳ ወር ይሁንልን ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.