Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

 

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ከተማ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ11 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋው ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ከ30 ላይ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው ወ/ሮ ቀለመወርቅ ት/ቤት አካባቢ የደረሰ ነው።

አደጋው አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲሱ ገበያ ወደ ፒያሳ ሲጓዝ ወ/ሮ ቀለመወርቅ ትምህርት ቤት አካባቢ ሲደርስ መንገዱን ስቶ እግረኛ መንገድ ላይ በመውጣቱ የደረሰ ነው፡፡

በዚህም ሁለት እግረኞች ህይወታቸው ሲያልፍ አንድ የአደጋው ሰለባ ሆስፒታል ከገባ በኋላ ህክምና እየተደረገለት ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል፡፡

እንዲሁም አሽከርካሪውን ጨምሮ 11 ተሳፋሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ÷የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.