Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች እና ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተጉዘው ከተገኙ አባቶች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ የሃይማኖት አባቶች በማኅበረሰብ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል።

ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር እየተደረጉ ያሉ ውይይቶች መቀጠላቸውን ገልጸው፤ ዛሬ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ተጉዘው በስብሰባው የተገኙትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባቶችን ተቀብለን ተወያይተናል ሲሉ ገልጸዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ሰላም እና ፀጥታን፣ የኅብረተሰቡን የልማት ፍላጎቶች፣ ቤተክርስቲያኒቷ ውስጥ ስላሉ የአስተዳደር ተግዳሮቶች ብሎም የሃይማኖት አባቶች ዘላቂ ሰላምን ለማረጋጥ የሚኖራቸውን ሚና አስመልክተው ጉዳዮችን መነሳታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.