Fana: At a Speed of Life!

በ500 ሚሊየን ዶላር ወጪ ያልተማከለ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዓለም ባንክ በተገኘ 500 ሚሊየን ዶላር ያልተማከለ የኤሌክትሪክ ኃይልና መብራት አቅርቦት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ዓለም ባንክ እና ውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለስድስት ዓመታት የሚተገበረው ይህ ፕሮጀክት÷ 3 ነጥብ 7 ሚሊየን ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ጌታቸው ዋቄ እንዳሉት÷ ፕሮጀክቱ የሚተገበረው ለማኅበረሰብ የቤት ውስጥ አገልግሎት እንዲሁም የማኅበራዊና የንግድ ተቋማትን የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማሻሻል ነው።

በከተማ እና የኤሌክትሪክ መስመር ባልተዳረሰባቸው የገጠር አካባቢዎችም ለቤት ውስጥ፣ ለንግድ እና ለማኅበራዊ አገልግሎት የሚውል የኃይል አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ የሚተገበር መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በማህሌት ተ/ብርሃን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.