Fana: At a Speed of Life!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶች ፎረም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለከፍተኛ ዓላማ” በሚል መሪ ሃሳብ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶች ፎረም በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡

በፎረሙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን ፥ የትምህርት ተግዳሮቶች ናቸው የተባሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴዔታ ኮራ ቱሹኔ (ተ/ፕ/ር) ፥ የጥራት ችግር፣ የምሩቃን ሥራ አጥነት፣ የመሰረተ ልማት አለመሟላት፣ የመምህራን እጥረትና የአመራር ብቃት ክፍተት በትምህርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ናቸው ብለዋል።

የተቋማት ልየታ፣ የራስ ገዝነት፣ የምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪ ትስስር እንዲሁም የዲጂታል ቴክኖሎጂን ለመማር ማስተማርና ለምርምር መጠቀም የዘርፉን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ እንደሚረዱ ተናግረዋል።

ተማሪዎች እውቀት እንጂ ክህሎት ይዘው አለመውጣታቸው በሥራ ቅጥር ወቅት ችግር እንዲገጥሟቸው ማድረጉንም አንስተዋል፡፡

ፎረሙ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ፥ የዘርፉ ተግዳሮቶች እንዲቀረፉ ይረዳሉ የተባሉ ጽሑፎች ቀርበው ምክክር እንደሚደረግባቸው ተጠቁሟል፡፡

በሙክታር ጠሃ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.