Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻልና ሐዋሳ ከተማ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 18ኛ ሳምንት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻልና ሐዋሳ ከተማ ድል ቀናቸው።

ምሽት 1:00 ላይ በተካሄደው የመቻል እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ መቻል ጨዋታው እንደተጀመረ ምንይሉ ወንድሙ በሶስተኛው እና አቤል ነጋሽ በስድስተኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች መቻል 2 ለ 0 አሸንፏል።

በተመሳሳይ ቀን 10:00 ላይ በተካሄደው የድሬዳዋ ከተማና የሐዋሳ ከተማ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሽንፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.