Fana: At a Speed of Life!

ባንኩ የሳይበር ጥቃት እንዳልደረሰበት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውስጥ ሲስተም ችግር እንጂ የሳይበር ጥቃት እንዳልደረሰበት አስታውቋል፡፡

ባንኩ ተቋርጦ የነበረው የኤቲኤም አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ስራ የጀመረ መሆኑን የገለጸ ሲሆን ፥ በቀጣይም ሁሉንም ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ሥራ እንደሚያስጀምር አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የተከሰተው የአገልግሎት መቋረጥ በባንኩ የውስጥ የሲስተም ችግር እንጂ በሀሰት እንደሚሰራጨው ከባንኩ ውጪ በደረሰ የሳይበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ጥቃት አለመሆኑን አረጋግጧል፡፡

ባንኩ አስተማማኝ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ ያለው መሆኑንም ነው ያስገነዘበው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ደንበኞች ምንም ዓይነት ስጋት እንዳይገባቸው አሳስቦ ፥ ችግሩን በሰዓታት ልዩነት ሙሉ በሙሉ ለማስተካከል እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.