Fana: At a Speed of Life!

የኤሌክትሪክ አገልግሎት የቆጣሪ ውል እድሳትን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም አራዘመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚያገለግል የቆጣሪ ውል የእድሳት ጊዜ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ማራዘሙን አስታውቋል፡፡

የውል እድሳቱን ከሕዳር 1 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ለማከናወን ታቅዶ ወደ ሥራ ቢገባም÷ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር መላኩ ታዬ ተናግረዋል፡፡

የውል እድሳቱ ቆጣሪ ከወሰዱ ከአምስት ዓመታት በላይ የሆናቸውን ደንበኞች ብቻ የሚመለከት መሆኑን አስገንዝበው÷ እድሳቱ ምንም አይነት ክፍያ እንደማይጠይቅ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ደንበኞች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማዕከል በመሄድ በተሰጠው የጊዜ ገደብ የውል እድሳቱን ማከናወን ይችላሉ ነው ያሉት፡፡

የውል እድሳቱ ቆጣሪን ለማይታወቅ አካል የሚያስተላልፉ ደንበኞችን ለመቆጣጠር፣ የኃይል ሥርቆትን ለማስቀረት እና የኃይል መቆራረጥ ችግርን ለማቃለል እንደሚያስችልም አብራርተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.