Fana: At a Speed of Life!

ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በኦሮሚያ ክልል ማያ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዲሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ፖለቲካና ርዕዮተ-ዓለም ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህን (ዶ/ር) ጨምሮ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በኦሮሚያ ክልል ማያ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተመለከተ።

መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ በመላ ሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች የመስክ ምልከታና ድጋፋዊ ክትትል በፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እየተደረገ ይገኛል።

መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎች ያሉ ሐብቶችና ጸጋዎችን በአግባቡ ለመጠቀም እንዲቻል፣ የሚነሱ ቅሬታዎችንም ከኀብረተሰቡ ጋር ተቀራርቦ ለመፍታት በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ሲሆን÷ የመስክ ምልከታና ድጋፋዊ ክትትል መርሐ-ግብሩም የዚህ ተግባር አንድ አካል መሆኑ ተጠቁሟል።

በኦሮሚያ ክልል ማያ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን የተመለከተው ቡድንም÷ በከተማው የተከናወኑ የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር፣ የመስኖና ሌሎች የልማት ሥራዎችን እንቅስቃሴ ጎብኝቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.