Fana: At a Speed of Life!

“የጦርነት ጥሩ የሠላም መጥፎ የለውም” – ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ በመቀጠል የተለያዩ የሰላም ፕሮግራሞችን ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

ፓርቲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ÷ ጦርነት መቼም ቢሆን የፖለቲካ ልዩነቶችን ለመፍታት የተሻለ አማራጭ እንዳልሆነ በአጽንኦት ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ በርካታ የሐይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ያሏት ሀገር በመሆኗ በእነሱ አለመግባባቶችን መፍታት እንደሚገባም ፓርቲው አስገንዝቧል፡፡

ፓርቲው በኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላም ለማስፈን የሚያደረገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በማረጋገጥ ለሰላም ስራ ፕሮግራም ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

የሰላም ሐሳቡ እንዲሳካም የሚመለከታቸው አካላትና ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.