Fana: At a Speed of Life!

ለአማራ ክልል 25 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው የደህንነት ካሜራዎች ድጋፍ ተደረጉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለአማራ ክልል 25 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው ዘመናዊ የደህንነት ካሜራዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ኢ/ር) በአማራ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የከተሞች መሠረተልማት ቢሮ ሃላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ/ር) አስረክበዋል፡፡

በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ወርቁ ጋቸና (ኢ/ር)÷ተቋሙ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መስክ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ተቋሙ ከተሞችን ስማርት ሲቲ ለማድረግ ሥራ መጀመሩን ጠቁመው÷ይህን ተግባር ወደ አማራ ክልል በማስፋት ከተሞችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

አሕመዲን መሐመድ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷የተበረከቱት ካሜራዎች በአማራ ክልል የከተሞችን ደህንነት ለማስጠበቅ  ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ አንስተዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ለዘርፉ ባለሞያዎች ስልጠናዎችን በመስጠትና የቴክኒክ ድጋፎችን በማድረግ ሚናውን እንደሚያጠናክር መገለጹንም የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.