Fana: At a Speed of Life!

የምሥራቅ አማራ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አማራ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት በወቅታዊ ጉዳዮችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እያደረገ ነው።

መድረኩ የአካባቢውን ሰላም ዘላቂ በማድረግ ረገድ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን በዝርዝር እንደሚገመግም ተመላክቷል፡፡

ከግምገማው በኋላም በቀጣይ ጊዜያት ተግባራዊ የሚደረጉ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ይጠበቃል መባሉን የደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ አመላክቷል፡፡

በመድረኩ ላይ÷ የአማራ ክልል ም/ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)፣ የሰሜን ምሥራቅ እዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አሰፋ ቸኮል፣ የደቡብ ወሎና ሰሜን ወሎ ዞኖች፣ የደሴ፣ ወልዲያና ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደሮች፣ የዋግ ኽምራ ዞን የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.