Fana: At a Speed of Life!

ሰሞኑን የተፈጠረውን ችግር እንደአጋጣሚ ተጠቅመው ደንበኞችን ሊያጭበረብሩ የሚሞክሩ አሉ – ባንኩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሞኑን የተፈጠረውን ችግር እንደአጋጣሚ በመጠቀም ሊያጭበረብሩ ከሚሞክሩ ግለሰቦች ደንበኞቹ ራሳቸውን እንዲጠብቁ አስጠነቀቀ፡፡

አጭበርባሪዎች ሰሞኑን ከሲስተም ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ችግር እንደ አጋጣሚ ለመጠቀም ሙከራ በማድረግ ላይ መሆናቸውን እንደደረሰበት ባንኩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

እነዚህ አጭበርባሪዎች በአብዛኛው ከባንክ የደወሉ በማስመሰል “የተዘጋ ሂሳባችሁን እንክፈትላችሁ”፣ “ሂሳባችሁ እንዳይዘጋ የምንልክላቹሁን ኮድ አስገቡ” የሚል የማጭበርበሪያ ዘዴ በመጠቀም የዘረፋ ሙከራ በማድረግ ላይ እንደሆኑም ጠቁሟል።

ሆኖም ግን ባንኩ ስልክ ደውሎ ስለ ሂሳብዎ መረጃ የሚጠይቅበት፣ ሂሳብ የሚከፍትበትም ሆነ የሚዘጋበት አሰራር እንዲሁም ደንበኞች እንዲጠቀሙበት የሚልከው ምንም አይነት ኮድ የለም ብሏል፡፡

በመሆኑም ማንኛውም የባንኩ ደንበኛ መሰል ሁኔታ ሲገጥመው ምንም ዓይነት እርምጃ ከመውሰድ በመቆጠብ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ አሊያም በ951 ለባንኩ የደንበኞች ጥሪ ማዕከል በመደወል ስለሁኔታው መረጃ መጠየቅ እንዳለበት አስገንዝቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.