Fana: At a Speed of Life!

ከ234 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ ተሽከርካሪዎች ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ገንዘብ ሚኒስቴር በ234 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የገዛቸውን 42 ቶዮታ ሃርድ ቶፕ የመስክ ተሽከርካሪዎችን ለ12 ክልሎች፣ ለሁለት ከተማ አስተዳደሮችና ለአራት የፌዴራል ተቋማት አስረከበ፡፡

ግዥው የተፈጸመው ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በገንዘብ ሚኒስቴር ተግባራዊ በሚደረገው “በኢ ኤስ ፒ ኢ አይ ፒ ኤፍ” ፕሮግራም በጀት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል በ171 ሚሊየን ብር የተገዙ 305 ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ 305 ዩፒ ኤሶች፣ 220 ፕሪንተሮች፣ 95 ጄኔሬተሮች እና 95 ወርክ ስቴሽን ኮምፒዩተሮች በሚቀጥሉት ቀናት ርክክብ እንደሚፈጸምም ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.