Fana: At a Speed of Life!

የብራዚል የቀድሞ ፕሬዚዳንት ከኮቪድ ክትባት ጋር በተያያዘ ክስ ተመሰረተባቸው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብራዚል የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጄር ቦልሶናሮ የኮቪድ ክትባት መረጃ በማጭበርበር ወንጀል በፖሊስ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

ቦልሶናሮ የኮቪድ 19 ክትባት በፈረንጆቹ 2021 በብራዚሏ ሳኦ ፖሎ ከተማ እንደወሰዱ የህክምና ማስረጃቸው ቢገልፅም፤ በተደረገባቸው ምርመራ በተጠቀሰው ዕለት በሳኦ ፖሎ ከተማ እንዳልነበሩ ተረጋግጧል፡፡

በተጨማሪም በተንቀሳቃሽ ምስል ያልተፈቀደ እንክብል በመወሰድ ብራዚላውያን ያልተረጋገጠ የኮቪድ 19 መድሃኒት እንዲወሰዱ በማድረግ ክስ የቀረበባቸው የቀድሞ ፕሬዚዳንቱ፤ ስለ ኮቪድ ክትባት መረጃቸው የሚያስታውሱት ነገር እንደሌለ ለፖሊስ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ፖሊስ በቦልሶናሮ እና በሌሎች ስምንት ሰዎች የውሸት የኮቪድ ክትባት የምስክር ወረቀት በመያዝ እና ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት እንዲሁም ለዜጎች የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ወንጀል ክስ መስረቶባቸዋል፡፡

የ68 ዓመቱ አዛውንት ጄር ቦልሶናሮ በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ከተባሉ የእስር ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተመላክቷል፡፡

እንደ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ብራዚል በፕሬዚዳንት ጄር ቦልሶናሮ የአመራር ዘመን ከ700 ሺህ በላይ ዜጎችን በኮቪድ ያጣች ሲሆን ከአሜሪካ በመቀጠል ብዙ ዜጎችን በቫይረሱ ያጣች ሀገር ሆና መመዝገቧን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.