Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ችግኝ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመጪው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ችግኝ የማዘጋጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል።

በቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምህረት እንደገለጹት÷ ለ2016 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አስፈላጊው እቅድ ተዘጋጅቶ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በዚህም በክልሉ ሁሉም ዞኖች ለቀጣዩ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ችግኝ የማፍላት ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

እስካሁን በተከናወነ ሥራም 400 ሚሊየን የሚጠጋ ችግኝ ለቆጠራ መድረሱን ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

እየተዘጋጁ ከሚገኙት ችግኞች መካከል ፍራፍሬዎችን ጨምሮ ዋንዛ፣ ወይራ፣ የሐበሻ ጽድ እና ሌሎች እንደሚገኙበት አስረድተዋል፡፡

ከችግኝ ዝግጅቱ ጎን ለጎንም የመትከያ ቦታ የመለየት ሥራ በማከናወን እስካሁን 125 ሺህ ሄክታር የተከላ ቦታ መለየቱን ጠቁመዋል፡፡

በተመሳሳይ ምን አይነት ችግኝ በየትኛው ቦታ ይተከላል እና መሰል ጉዳዮች መለየታቸውን አቶ እስመለዓለም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ለመትከያ አገልግሎት ለሚውሉ ቦታዎች የካርታ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን የማዘጋጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.