Fana: At a Speed of Life!

ከአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የሚነሱ አሉባልታዎች መሰረተ ቢስ ናቸው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የሚነሱ አሉባልታዎች መሰረተ ቢስ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

 

በመዲናዋ እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችን አስመልክቶ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህ ወቅት÷ በከተማዋ እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት ከተማዋን ወደ ተሻለ የከተማነት ደረጃ ለማሸጋገር መሰረታዊ ስራ መሆኑን ከንቲባዋ አመልክተዋል።

በልማት ሂደቱ ከአካባቢያቸው ተነሺ የሆኑ ዜጎችን ከተማ አስተዳደሩ በካሳ እና ምትክ ቦታ በመስጠት በተገቢው እያስተናገደ መሆኑን የገለፁት ከንቲባዋ፤ ሂደቱ የፍትሃዊነት ችግር እንዳይኖረው ጥንቃቄ መደረጉንም ገልፀዋል።

የኮሪደር ልማቱ ካለፈው ዓመት ግንቦት ወር ጀምሮ ጥናት የተደረገበት መሆኑም የተገለፀ ሲሆን÷ ከተማ አስተዳደሩም በልማቱ ዙሪያ የአካባቢውን ህብረተሰብ ማወያየቱን ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በልማት ተነሺዎች የሚነሱ ቅሬታዎች ካሉ ግን ለማስተናገድ የቅሬታ ፅ/ቤት ስለማቋቋሙም ተናግረዋል፡፡

የፒያሳን አካባቢ በሚሸፍነው የኮሪደር ልማት ጋር ተስማምተው እንዲሰሩ የተለዩ 6 ቅርሶች መለየታቸውንም ተገልጿል።

አጠቃላይ ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ይሰራል የተባለ ሲሆን÷ መልሰው እየተሰሩ ያሉ የመንገድ ልማቶች ግን ከወዲሁ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ተብሏል።

ለአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ህብረተሰቡ እያደረገ ላለው ትብብር ምስጋናቸውን ያቀረቡት ከንቲባዋ ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

 

በዉብርስት ተሰማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.